top of page

ታሪከ ነፀር - የመጽሐፍ ምረቃ ከጸሃፊ ሽፈራው ዕንቁባሕሪይ ጋር

Sat, Dec 06

|

Sankofa Video, Books & Cafe

ከጸሃፊ ሽፈራው ዕንቁባሕሪይ ጋር "ታሪከ ነፀር" በተሰኘው የታሪክ መጽሐፍ ዙሪያ ያዘጋጀነውን ምርቃት በሳንኮፋ ተገኝተው እንዲካፈሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።

Tickets are not on sale
See other events
ታሪከ ነፀር - የመጽሐፍ ምረቃ ከጸሃፊ ሽፈራው ዕንቁባሕሪይ ጋር
ታሪከ ነፀር - የመጽሐፍ ምረቃ ከጸሃፊ ሽፈራው ዕንቁባሕሪይ ጋር

Time & Location

Dec 06, 2025, 3:00 PM – 7:00 PM

Sankofa Video, Books & Cafe, 2714 Georgia Ave NW, Washington, DC 20001, USA

Guests

About The Event

እነሆ ታሪክ ነፀር!


የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሰንደቅ ዐላማ ለሚመለከት፤ የኅብረ ቀለማቱ ስምረት፤ ዐይንን ወይም ትኩረትን የመሳብ ኃይሉን ይገነዘባል። የዚህ ሚስጢሩ ግን፣ ዐይን ከሚመለከተው በላይ ረቂቅነት አለው። የሰው ዘር ይቺን ረቂቅነቷን ጥልቅ የሆነች ጥንታዊቷን በደመነፍስ ይውቃታል።ነገር ግን፣ ዬት እንደሚያውቃት ረስቷታል። የሰው ዘር ሰንደቅ ዐላማዋን ያያት፣ የሰው ልጅ ከተፈጠረባት፤ንተወልዶ ካደገባት፤ ከገነት ምድር፤ ከእግዚአብሔር ቤት እንደነበር በትክክል ቦታውን ባያስታውሰውም፤ በደመነፍስ ሲያሰላስል ኖረ። ቦታው ዬት እንደሆነ ለማስታወስ፤ የሰው ዘር ኢትዮጵያ መወለዱን ዘንግቶ፤ ከዬት መጣሁ? እያለ ሲመራመር ኖረ። ኢትዮጵያ መወለዱን ዘንግቶ፤ ከዬት መጣሁ? እያለ ሲመራመር  ኖረ። ኢትዮጵያ የመወለዱ ምሥጢር በደሙ መመዝገቡን ሳያውቀው ኖረ። 


በቅርብ በዓለም የሚገኘው የሰው ዘር የደም ናሙና ተመረመረ። በምርመራውም፤ በደሙ የተመዘገበው የጅኑ ዘመረል (ዴኤኔ) ሲነበብ፣ ኢትዮጵያ መወለዱ ተበሰረ። እኛም ኢትዮጵያ የተወለድንበትን ልዩ ቦታ ለማወቅ እጅግ ብዙ ጣርን። የዓለም የጥንት መዛግብትን በተቻለን ሁሉ መረመርን። የሸክላ፣ የድንጋይ፣ የደንገል ልፍፍ ጽሑፎችን አመሳከርን። ዕውነውቱን ከትውፊቱ፣ ተረቱን ከንግርቱ፣ አማርጠን ለየን። 


ሳይንቲስቶቹ ሰው ከ 300,000 ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ዓለም መሠራጨቱን አረጋገጡልን። ኢትዮጵያ ከዬትኛው ቦታ ተነስቶ እንደሄደማመላከቻውን ሁሉ ተከታትለን በመጨረሻም ዓባይ ራሱ ተለዋጭ ስሙ ዕንቁባሕርይ እንደሆነ፤ የዕንቁ ባሕሪይ ሌላው ተለዋጭ  ስሙ እግዚአብሔር እንደሆነ፤ የእግዚአብሔር ቅዱስ ደብሩ ዕንቆደር እንደሆነ ግልጽ ሆነልን። ዕንቆደር ሰው የተፈጠረባት ምድር፤ የሰማይና ምድር መገናኛ አውታር የተተከለባት ደብር፤ የገነት ዛፍ የበቀለባት ኤደን፤ የአማልክት መመላለሻ በር፤ የመንግስተ ሰማየት ዓርማ አረንጓዴ፣ ብጭ እና ቀይ ኅብረ ቀለም ሰንደቅ ዓላማ የተተከለባት ዕንቆደር/ጎንደር እንደሆነ ዕውን ሆነ። እስከዛሬ ያልተገለጠው ምስጢር ይህ ነበር። እነሆ! ዛሬ ምሥጢሩ በታሪክ ነፀር ተገለጸ። 


ደራሲው

Share This Event

bottom of page