Book Event - "Be-Ente Ethiopia" Book Launch, and Discussion
Sun, Sep 08
|Sankofa Video, Books and Cafe
Join us 6pm Sunday, September 8th, for Wondimu Geda's new Amharic book "Be-ente Ethiopia" launch, followed by a discussion!


Time & Location
Sep 08, 2024, 6:00 PM – 8:00 PM
Sankofa Video, Books and Cafe, 2714 Georgia Ave NW, Washington, DC 20001, USA
About The Event
ስለ 'በእንተ ኢትዮጵያ' ከወንድሙ ገዳ
‘በእንተ* ኢትዮጵያ’ ብዬ በሰየምኩት በዚህ መጽሐፍ በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያን ፖሊቲካዊ፣ ማህባራዊና ባህላዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በተሰሙኝ ስሜቶችና በታዩኝን እውነታዎች መሰረትነት እነዚኽኑ ለመዳሰስ፤ ለማኄሳ፤ ለመጠየቅና ለመሞገት ተሞክሯል፡፡ አንደኛው የጽሑፉ ግብ የውይይት መነሻሀሳቦችንና ጥየቄዎችን ለአንባብያን፣ ለሕዝቡና ጉዳዮቹ በተለይ ለሚመለከቷቸው አካላት ማቅረብ ነው፡፡ በሀገራችን እየደረሱ ላሉ ውስብስብ ችግሮች በየዘመኑ የተፈራረቁ መንግስታት ዋነኛ የኃላፊነት ድርሻ እንደተጠበቀ ሆኖ ለገባንበት የተግዳሮት አዙሪት ተጠያቂው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ተጨባጭ መፍትሄውም (ጣት ከመጠቋቆም፣ እልህ ከመጋባትና ከመበሻሸቅ
ባሻገር) የእያንዳንዱ ዜጋ የድርሻውን ማዋጣትና ተግባራዊ ሀላፊነቱን መወጣት ነው የሚለው ዋነኛ የመጽሐፉ ማጠንጠኛ ሀሳብ ነው፡፡ ከጥንት እስከአሁን ያሉና የነበሩ የፖለቲካ መሪዎቻችንም ሆኑ ምሁራን ለጥፋት በለው ልማት ከሌላ አለም የተላኩብን ባእድ ፍጡራን ሳይሆኑ የባህሎቻችንና የፍልስፋናዎቻችን ውልደቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም የጽሑፍ አንዱ መነሻ ሀሳብ አምባገነን መንግስታት ብቻቸውን ይህንን የተግዳሮት አዙሪት ሊያስቀጥሉ አይችሉም የሚል ነው፡፡ ‘እንንቃና ለመፍትሄዎች እንሰባሰብ፤ ባለአፍሮ አይገባ መስቀል ቄስ፣ የነገር ውል አራቂ ወልይ፣ ግጭት ፈቺ አበጋር፣ አዋቂ አስታራቂ አባቦኩ፣ ልበብር እመምኔት፣ የበቁ ሸሆይ፣ ጉምቱው ቃዲ፣ የነቃሽ ዱበርቲ፣ የተምታቱ…